ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጋሞ ዞን ጨንቻ ከተማ በመገኘት የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል

409

ጥቅምት 23/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በጋሞ ዞን ጨንቻ ከተማ በመገኘት የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማው በህብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው የሽመና ስራ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን ስራ ተመልክተዋል በተጨማሪም በጨንቻ ከተማ የተቀናጀ የግብርና ስራንም ተመልክተዋል ።

በዚህም በአነስተኛ መሬት አፕልን ጨምሮ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን የሚያለማ ግለሰብ ማሳን ጎብኝተዋል።

ይህን አይነት ስራ በሁሉም አካባቢዎች እንዲስፋፋም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሳሰቡት።

በጋሞ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያ እየተከናወነ ያለውን ማህበረሰብ አቀፍ ስራንም ተመልክተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም