ቀጥታ፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋን በየፈርጁ መታደሏን ከሚያሳዩን ሥፍራዎች አንዱ የጎፋ ዞን ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

ጥቅምት 23/2015 (ኢዜአ) ሀገራችን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋን በየፈርጁ መታደሏን ከሚያሳዩን ሥፍራዎች አንዱ የጎፋ ዞን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ከዞኑ አልፎ ክልሉን ለማልማት የሚያስችል ያልተነካ ዐቅም እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ባለ ግርማ ሞገሱ ወይላ ተራራም በውስጡ የያዘው ብዝኃነት የሀገራችን የኢትዮጵያ ማሳያ ያደርገዋል ነው ያሉት።

የዶጫ ደምበላ አርሶ አደሮች በ80 ሄክታር ላይ ያመረቱት ሰሊጥ፣ ማሾ፣ አኩሪ አተር፣ ጤፍ እና ፍራፍሬም አካባቢው የተፈጥሮ በረከት እንደተቸረው የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም