በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
ጥቅምት 22 2015(ኢዜአ) በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በግጭት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ።
በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በኦታዋ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
ዳያስፖራው ለኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አምባሳደር ፍጹም ጥሪ አቅርበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በካናዳ የሚገኘው ኤምባሲ ዳግም በመከፈቱ ደስታቸውን ገልጸው በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የጀመሩትን ጥረት በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ገንዘብ ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ ብቻ በመላክም ለኢኮኖሚያዊ ግንባታና ለሰላም አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን ለሌሎችም በተመሳሳይ ይሄን ተግባር ለመፈጸም እንዲተጉ ጠይቀዋል።
አምባሳደር ፍጹም በካናዳ አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ከዳያስፖራው ጋር ያደረጉት የመጀመሪያ ውይይት ውጤታማ እንደነበር ገልጸው ለተሳተፉት ወገኖችም ምስጋና አቅርበዋል።