ቀጥታ፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሰባት መምህራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

ጥቅምት 21 ቀን 2015 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራር ቦርድ ለሰባት መምህራኑ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።

የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ ከመቅረቡ በፊት በሀገር ውስጥና ውጭ ባለሞያዎች ተገምግሞ፣በዩኒቨርሲቲው ሴኔት እና በሚያስተምሩበት ትምህርት ክፍል ተቀባይነትን አግኝቶ የተሰጠ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረጉን ያገኙ መምህራን ዶክተር ስዩም ለታ ፣ዶክተር ሀሰን ማሞ ፣ዶክተር ፈለቀ ዘውገ ፣ዶክተር ግርማ ስዩም፣ዶክተር ጉርጃ በላይ ፣ዶክተር አሰፋ አበጋዝ እንዲሁም ዶክተር ተሻለ ሶሪ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም