ቀጥታ፡

የአበበች ጎበና የህጻናት ክብካቤና ልማት ማህበር በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 146 ሴቶች አስመረቀ

ጥቅምት 19 ቀን 2015 (ኢዜአ)  የአበበች ጎበና የህጻናት ክብካቤና ልማት ማህበር በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 146 ሴቶች አስመረቀ።

ማህበሩ ለ34ኛ ጊዜ አሰልጥኖ ያስመረቃቸው ሴቶች በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ተመራቂዎቹም በሰዎች ለሰዎች መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ድጋፍ በባህላዊ እና ዘመናዊ ምግብ ዝግጅት፣ በመስተንግዶ፣ በቤት አያያዝና በጤና አጠባበቅ ለስድስት ወራት የሰለጠኑ መሆናቸውም ተመላክቷል።

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጌታቸው ዘውዴ ድርጅቱ የሴቶችን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በማህበሩ በኩል ያገኙት የሙያ ስልጠና በቀጣይ ወደ ስራ ለመግባት ሰፊ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ሰልጣኞቹ ተናግረዋል።

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላደረገላቸው ድጋፍ እና የአበበች ጎበና የህጻናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር ስልጠና በመስጠት ላደረጉት ቀና ተግባር አመስግነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም