በህብረት ስንሠራ የምግብ ዋስትና ግባችን ይሳካል፣ ፈተናዎቻችንን ድል እንነሳለን፣ ሀገራችንም ትለማለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

11

ጥቅምት 19 ቀን 2015 (ኢዜአ) በህብረት ስንሠራ የምግብ ዋስትና ግባችን ይሳካል፣ ፈተናዎቻችንን ድል እንነሳለን፣ ሀገራችንም ትለማለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳና ቦራ ወረዳ፣ ስምንት ሺህ አርሶ አደሮች በ31 ሺህ ሄክታር ላይ በኩታ ገጠም ያለሙትን ግብርና ጎብኝተዋል።

አርሶ አደሮቹ በስኬታማነት ስንዴን አምርተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህብረት ስንሠራ የምግብ ዋስትና ግባችን ይሳካል፣ፈተናዎቻችንን ድል እንነሳለን፣ ሀገራችንም ትለማለች ነው ያሉት በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም