ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ሰሜን መቄዶኒያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ጥቅምት 18 ቀን 2015 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ና ሰሜን መቄዶኒያ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።

አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ለሰሜን መቄዶኒያ ፕሬዝዳንት ስቴቮ ፔንድሮቭስኪ የሹመት ደብዳቤአቸውን አቀረቡ።

በእለቱም ሁለቱ ሀገራት የነበራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በሚያሳድጉ ጉዳዮችና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል።

አምባሳደር ደሚቱ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ ለፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይ በደቡብ አፍሪካ ስለተጀመረው የሰላም ሂደት አብራርተውላቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሂደቱ ያለውን ቁርጠኝነት የገለጹት አምባሳደሯ መንግስት በትግራይ ክልል ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

የሰሜን መቄዶኒያ ፕሬዝዳንት ስቴቮ ፔንድሮቪስኪ በበኩላቸው የኢትጵያ መንግስት ለሰላም ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀው በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው የሰላም ሂደት በስኬት እንደሚጥናቀቅ አምነታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም