ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገጹ አስታወቀ

ጥቅምት 17 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ከቁጥጥሩ ውጭ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገጹ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው ደንበኞች እንዲሁም የገጹ ተከታታዮች በፌስቡክ ገጹ የሚተላለፉ ማንኛውም መልዕክቶች የአየር መንገዱ አለመሆኑንም ገልጿል፡፡

አየር መንገዱ አክሎም ችግሩን ለመፍታት በአሁኑ ሰዓት ከሜታ ኩባንያ ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም