ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፈቱ

361

ጥቅምት 17/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በመዲናዋ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መርቀው ከፈቱ።

በተለምዶ "15 ሜዳ" ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ከዚህ ቀደም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ አልነበረም።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዲስ መልኩ ተገንበቶ በመጠናቀቁ በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ።

የስፖርት ማዘውተሪያው ግንባታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ የተገነባ በመሆኑ የቀደመ አግልግሎቶቹን ይሰጣል።

የስፖርት ማዘውተሪያው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመርቆ ሲከፈት ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።

የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራው ግንባታ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮጀክት አካል መሆኑም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም