ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት "ኢትዮጵያ አያሸነፈች ትሻገራለች" በሚል መሪ ቃል በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት "ኢትዮጵያ አያሸነፈች ትሻገራለች" በሚል መሪ ቃል በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ እየተካሄደ ነው

ጥቅምት 15/2015 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀው 12ኛው ስለ ኢትዮጵያ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ "ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።

የፎቶ ግራፍ አውደርዕይና የፓናል ውይይቱን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሌ ሀሰን መርቀው ከፍተዋል።

የ12ኛው ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት "ልማት በተግባር ስለ ኢትዮጵያ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጓል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እና ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ የመነሻ መወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከዚህ ቀደም የውጭ ሃይሎችና ተላላኪዮቻቸው ኢትዮጵያን ለመበተን ሰላምና ጸጥታን ሲያደፈርሱ የነበረበት አካባቢ ቢሆንም አሁን በሰፈነው ሰላም "ስለ ኢትዮጵያ " የፓናል ውይይት መድረክ በዞኑ ግልገልበለስ ከተማ መካሄድ ችሏል።
በመድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፌደራል፣ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል እና ከአማራ ክልል የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።