“የእሳት ቀለበት፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ንፍቀ መዋዕል” መጽሐፍ ተመረቀ

183

ጥቅምት 15/2015 (ኢዜአ) በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ባለቤትነት የተዘጋጀና በተለያዩ ጻህፍት የተጻፈው “የእሳት ቀለበት፤ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ንፍቀ መዋዕል” የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ተመርቋል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የቀድሞ ጦር አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተመረቀው መጽሐፉ በታሪክ ባለሙያዎች ዳሰሳ እየተደረገበት ይገኛል።

መፅሐፉ በተለይም በሰራዊቱ ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊትና የጀግናው መከላከያ ሰራዊትን የሕግ ማስከበር ታሪኮችን በተለያዩ ታሪካዊ ዳራዎች አስደግፎ ይዳስሳል።

ዛሬ የተመረቀው በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለው መጽሐፉ 360 ገፆች ያሉት የመጀመሪያው ቅፅ ሲሆን ቀጣይ ሁለት ቅፆች እንደሚዘጋጁ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም