የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ነገ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ነገ ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ መስከረም 14/2011 የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ነገ ይካሄዳሉ። ነገ የሚደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታዎች በ2010 ዓ.ም መጠናቀቅ ሲኖርባቸው የተራዘሙ ውድድሮች ናቸው። በሩብ ፍጻሜው ሲዳማ ቡናን በመለያ ምት ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጅማ አባጅፋር ጋር የሚጫወት ይሆናል። ኢትዮጵያ ቡናና መከላከያም የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አሸናፊ ክለቦች መስከረም 19 ቀን 2011 ዓ.ም የፍጻሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። የውድድሩ አሸናፊ ክለብ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን ወክሎ ይካፈላል።