ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በእንጦጦ የስነ ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ኤግዚቢሽን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በእንጦጦ የስነ ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ኤግዚቢሽን ጎበኙ
ጥቅምት 14/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በእንጦጦ የስነ ጥበብ ማዕከል የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ኤግዚቢሽን መጎብኘታቸው ተገለጸ።
ኤግዚቢሽኑ የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በቨርቹዋል የሚያስጎበኝ ነው።
ይህ መስከረም ወር ላይ የተከፈተው ኤግዚቢሽን አዲስ አበባ ላይ በመሆን የላልይበላን ውቅር አብያተ ክርስቲያንት በአካል ተገኝቶ የመጎብኘት ያክል ምስል ከሳች በሆነ መንገድ ለመጎብኘት የሚያስችል ነው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው አውደርዕዩ በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።
በአውደርዕዩ በዋናነት ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ እንዴት እንደተገነቡ፣ ውስጣዊና ውጫዊ ገፅታቸውን ከምስል በተጨማሪ በድምፅ ዳብሮ የቀረበ መሆኑ ተመላክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ወቅት ያለውን የማለም አቅም የሚያሳይ እንደሆነ አስታውቀዋል።
አንድ ሰው ያለመውን ህልም በጋራ ወደ መሬት አውርዶ እውን አድርጎ የማሳየት አቅም እንደዚሁ የሚንፀባረቅበት እንደሆነ ነው የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኤግዚቢሽኑን ኢትዮጵያዊያን መጥተው እንዲመለከቱም ነው ጥሪ ያቀረቡት።