ቀጥታ፡

“የእናት አገር ጥሪ” በሚል ከተዘጋጀ የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ከ73 ሺህ ዩሮ በላይ ገንዘብ ተሰበሰበ

ጥቅምት 14 ቀን 2015 (ኢዜአ) “የእናት አገር ጥሪ” በሚል ከተዘጋጀ የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ከ73 ሺህ ዩሮ በላይ ገንዘብ ተሰበሰበ።

“የእናት አገር ጥሪ” በሚል ገቢ የተዘጋጀ የበይነ መረብ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ዝግጅት ትናንት ተካሄዷል።

መርሐግብሩን ያዘጋጁት የሮም የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ፣ በጣሊያን የዲፌንድ ኢትዮጵያ አስተባባሪዎችና በጣልያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጋራ በመተባበር ነው።

ድጋፉ የተሰበሰበው በጣልያን፣ግሪክና ማልታ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆኑን አስተባባሪዎቹ ጠቁመዋል።

ከመርሃ ግብሩ ከ73 ሺህ ዩሮ በላይ መሰብሰቡን እና የተሰበሰበው ድጋፍም በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ የሚውል መሆኑን ተገልጿል።

በዝግጅቱ በጣልያን፣ ግሪክና ማልታ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትወልደ-ኢትዮጵያውያውን ከ73 ሺህ ዩሮ በላይ የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን በጣልያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በየአካባቢያቸው በጋራ እና በተናጠል ሆነው ጨረታዎችን በመሳተፍ እንዲሁም ቀጥታ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ገልጿል።

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ዳያስፖራው አገር ስትጣራ ሁሌም አለን በማለት ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

አርቲስት ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) በበኩሉ ለኢትዮጵያ ምንም አይነት የምንቆጥበው ጉልበትም ሆነ ገንዘብ የለም፤ በጋራ ከቆምን ችግሮቻችንን እንሻገራለን ብሏል።

ትልቅነት አንድ ከመሆን ብቻ የሚገኝ እንደሆነም ገልጿል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን በዘርፈ ብዙ ጫናዎች እያለፈች ለምትገኘው አገራቸው ለምትፈልገው ድጋፍ ምላሽ መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ኤምባሲው በመግለጫው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም