የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ - ኢዜአ አማርኛ
የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ የሚባሉ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል።
ይህንን ሲያደርግም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተሞች ውጊያ ሳይደረግ የህወሓትንወታደራዊ ዐቅም ለማሽመድመድ የሚያስችል ስልት ተጠቅሟል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰብአዊ የርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በተቆጣጠራቸውአካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ እየሠራ ይገኛል።
የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በእነዚህ አካባቢዎች አገልግሎት ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት እንዲያፋጥኑ እያደረገ ነው።
ከየአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመነጋገር ሕዝባዊ አስተዳደር የሚቋቋምበትንና ማኅበራዊአገልግሎቶች የሚጀምሩበትን መንገድ እያመቻቸ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኅብረት በኩል በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግርየሚሳተፍ ይሆናል።
አጋጣሚውንም የሰላም ንግግሩን ግጭቱን በሰላም ለመፍታት የሚቻልበት ዕድል አድርጎ ይመለከተዋል።በመከላከያ ኃይላችን መሥዋዕትነት እየተስተካከለ የመጣውን ሁኔታ የበለጠ ለማጠናከር ምቹ አጋጣሚ የሚፈጥሮ አድርጎ ይወስደዋል።
በሰላም ንግግሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ የልኡካን ቡድን ዛሬ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ አምርቷል።
ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ምአዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት