ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም በነጩ ቤተ መንግስት ዙሪያ ሰልፍ አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም በነጩ ቤተ መንግስት ዙሪያ ሰልፍ አካሄዱ
ጥቅምት 14 ቀን 2015 (ኢዜአ) በርካታ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዋሽንግተን ዲሲ በነጬ ቤተመንግስት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የውጭ ጫናን ለመመከት የድጋፍ ደማቅ ሰልፍ አካሂደዋል።
አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወሙ መልእክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።
አሜሪካ በኢትዮጵያና በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ የምትከተለውን የተሳሳተ የውጭ ጉዳይ ፖሊስ ዳግም ልታጤነው እንደሚገባ የሚያሳስቡ መልእክቶች በሰልፉ ላይ የተስተዋሉ ሲሆን ሰልፉ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው ያላቸውን አጋርነት ያሳዩበት መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ሰልፉ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር ዲሲ ግብረ ኃይል በአሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት፣ ከተለያዩ ተቋማትና ወዳጆች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።