ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
ጥቅምት 14 2015 (ኢዜአ) የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል።
ሐዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ከቀኑ 7 ሰአት፤ ኢትዮ-ኤሌትሪክ ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 10 ሰአት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ይጫወታሉ።
ነገ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 10 ሰአት የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ከሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ቀደም ብሎ ከቀኑ 7 ሰአት ወልቂጤ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የአምስተኛ ሳምንት መርሐግብር እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል።
የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ12 ነጥብ ሲመራ፤ ኢትዮጵያ መድን በዘጠኝ ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ሰባት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ድሬዳዋ ከተማ፣ወላይታ ድቻና ሲዳማ ቡና ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የቅዱስ ጊዮርጊሱ ቶጓዋዊ የፊት መስመር ተጫዋች ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በስምንት ግብ እየመራ ነው።
የወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ፣የአርባምንጭ ከተማው ተመስገን ደረሰ፣የአዳማ ከተማው ዳዋ ሆቴሳና የሐዋሳ ከተማው ሙጂብ ቃሲም በተመሳሳይ ሶስት ግቦች ይከተላሉ።