በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአጋሮ ከተማ የተገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ

22

ጥቅምት 13/2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት አማካኝነት በአጋሮ ከተማ የተገነባውን የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ።

ጽህፈት ቤቱ ፋብሪካውን ያስገነባው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሂቤይ ፒንግል ማሽነሪስ ከተሰኙ ኩባንያዎች ጋር በአጋርነት ነው።

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ 300 ሺህ ዳቦና 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም አለው።

May be an image of 5 people

ፋብሪካውን ገንብቶ ለማጠናቀቅ 7 ወራትን መውሰዱም ተገልጿል።

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት በ11 ከተሞች ተመሳሳይ አቅም ያላቸው ዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎችን በጋራ ለመገንባት ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ጋር ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፤ ስምምነቱን ተከትሎ በአጋሮ ከተማ የመጀመሪያ ፋብሪካውን አስመርቋል ::

የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከዚህ ቀደም በመዲናዋ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቀን 1 ሚሊዮን ዳቦ የሚያመርት ፋብሪካ ማስገንባቱ ይታወሳል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም