የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መረጃን ተደራሽ በማድረግ ለሚያበረከተው አስተዋፅኦ የምስጋና ሽልማት ተበረከተለት - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መረጃን ተደራሽ በማድረግ ለሚያበረከተው አስተዋፅኦ የምስጋና ሽልማት ተበረከተለት
ጥቅምት 13/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መረጃን ተደራሽ በማድረግ ለሚያበረከተው አስተዋፅኦ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምስጋና ሽልማት ተበረከተለት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት /ኢዜአ/ ዜናና ዜና ነክ መረጃዎችን በተለያ ቋንቋዎች በማዘጋጀት በአገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጋል።
ትናንት ምሽት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምስጋና ሽልማት የተበረከተለት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ በዘርፉ በሚሰሩ ስራዎች ባከናወነው መረጃን ተደራሽ የማድረግ ተግባር ነው።
ኢዜአ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰብሳቢነት በተመሰረተውና የተለያዩ ተቋማትና ባለሙያዎችን በያዘው የውሃ ዲፕሎማሲ እና የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትም አባል በመሆን የራሱን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል።
ሽልማቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ለኢዜአ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ አስረክበዋል።
ከኢዜአ በተጨማሪ ሌሎች በዘርፉ መረጃን ተደራሽ እያደረጉ ያሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንም በተመሳሳይ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።