ቀጥታ፡

ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ስኬት የዜጎች ጥረትና የመልማት አቅም ወሳኝ በመሆኑ በሁሉም መስክ መትጋት ይገባል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

ጥቅምት 13/2015/ኢዜአ/ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ስኬት የዜጎች ጥረትና የመልማት አቅም ወሳኝ በመሆኑ በሁሉም መስክ ራሷን የቻለች ነጻ አገር ለመገንባት መትጋት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን እንዲሁም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተከነወኑ የልማት ስራዎችን ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ጎብኝተዋል።

May be an image of 8 people, people standing, fruit and outdoors

በአካባቢው በተለይም በሻይና በሩዝ ልማት አስደናቂ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይ ዓመት በሩዝና የሻይ ምርት ከአገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ስኬት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚሳካው በዜጎች ጥረት፣ ባለን ምቹ የመልማት አቅምና የተፈጥሮ ሃብት ነው ሲሉም አብራርተዋል።

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት፣ በቡና እንዲሁም ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች የተመለከቱት አስደናቂ ስራ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ምሳሌ ይሆናል ብለዋል።

ከዚህ በመነሳት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢያቸውን እምቅ አቅም በመረዳት ማልማት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በጅማ ዞን በክላስተር እየለማ ያለው የሩዝ ምርት አስደሳች መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሻይ ልማትም ለአገር ውስጥ በቂ ፍጆታ እየተመረተ መሆኑን በመመልከታቸው አድንቀዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ዓመት ሁለቱንም ምርቶች ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በሚያስችል መልኩ ለማምረት ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም