የኢትዮጵያ ማህበራዊና ባህላዊ ውቅር አጥፍቶ ጠፊ የሆነው አሸባሪው ሕወሓት ከፈጠራቸው ችግሮች እጅጉን የባሱ ፈተናዎችን በመሻገር የዘለቀ ነው- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ማህበራዊና ባህላዊ ውቅር አጥፍቶ ጠፊ የሆነው አሸባሪው ሕወሓት ከፈጠራቸው ችግሮች እጅጉን የባሱ ፈተናዎችን በመሻገር የዘለቀ ነው- አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
ጥቅምት 12 ቀን 2015 (ኢዜአ) “የኢትዮጵያ ማህበራዊና ባህላዊ ውቅር አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከፈጠራቸው ችግሮች እጅጉን የባሱ ፈተናዎችን ተሻግሮ የዘለቀና ጠንካራ መሰረት ያለው ነው” ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ።
“የኢትዮጵያ ማህበራዊ ስሪት እየፈረሰ በሚል የሚሰጡ አስተያያቶች መሰረተ ቢስና ከእውነታ የራቁ ናቸው” ብለዋል አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
“ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያ ማህበራዊና ባህላዊ ውቅር አጥፍቶ ጠፊ የሆነው አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ከፈጠራቸው ችግሮች እጅጉን የባሱ ፈተናዎችን በመሻገር የዘለቀና በጠንካራ መሰረት ላይ የተቀመጠ ነው” ብለዋል አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
ከሰብአዊ ጉዳዮች አኳያ የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ ተደራሽነትን ለማሳለጥ አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ አዳዲስ የሰብአዊ እርዳታ መተላለፊያ መንገዶችን መክፈቱን ቋሚ መልዕክተኛው ገልጸዋል።
የምግብ እርዳታ ስርጭት በድጋሚ መጀመሩንና አሸባሪው ሕወሓት በድብቅ ያስቀመጠውን የምግብ ክምችት ካለበት ቦታ በማውጣት ለዜጎች እየተከፋፈለ እንደሚገኝ አመልክተዋል።