የአሸባሪውን ህወሓት ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማ እና የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ሃዋሳ፣ አላባና ዳማና ከተሞች እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአሸባሪውን ህወሓት ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማ እና የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ሃዋሳ፣ አላባና ዳማና ከተሞች እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፣ሀላባ ና አዳማ ጥቅምት 12/2015 (ኢዜአ) በሃዋሳ፣ሀላባና አዳማ ከተሞች የአሸባሪው ህወሓት ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማንና አንዳንድ ምዕራባዊያን ለሽብር ቡድኑ በመወገን በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ ለመፍጠር እያደረጉ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የሲዳማ ክልል ሕዝብ የአሸባሪውን ህወሓት ሀገር የማፍረስ እኩይ ዓላማንና አንዳንድ ምዕራባዊያን በኢትዮጽያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ የሀዋሳ ከተማንና አካባቢዋን ጨምሮ ከሲዳማ ክልል ወረዳዎች የተውጣጣ በርካታ ህዝብ የተቃውሞ ድምፅን በህብረት እያሰማ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ በኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ሉዓላዊነት ላይ በውጭና በውስጥ ጠላቶች የሚደረግ የትኛውንም አይነት ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ መፈክሮችን በማሳማት ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።
ኢትዮጵያ ነጻነቷንና ክብሯን ጠብቃ ለዘመናት የኖረች ሀገር በመሆኗ አሁን በምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት እየተካሄደ ያለው ጫና ተቀባይነት የለውም ብለዋል ።
መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር እያደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ ጥረት እንደሚደግፉና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛንም ጣልቃ ገብነትን እጥብቀው እንደሚቃወሙ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ለሽብር ቡድኑና ያልተገባ ጫና በሚያሳድሩ ምዕራባውያን ላይ እያሰሙት ያለው የተቃውሞ ድምፅ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ትክክለኛ ምላሽ የሚስጥበትና ለማስጠንቀቅም ጭምር እንደሆነም ገልጸዋል።
በተለይ አሸባሪው ህወሓትና ተባባሪ የሀገር ውስጥ ባንዳዎች እንዲሁም አንዳንድ የውጭ ኃይሎች በሀገራችን ላይ እየፈጸሙ ያለውን እኩይ ተግባር በተባበረ ክንድና በአንድነት እንደሚያመክኑት አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ በሀላባ ከተማ ”ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል የምዕራባውያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በሰልፉ ከሀላባ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አርሶ አደሮችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ነዋሪዎች ተሳፊ ሆነዋል።
ሰልፈኞቹ ምዕራባውያን በአሸባሪው ህወሓት ላይ የያዙትን የወገንተኝነት አቋምና በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጫና የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ ነው።
ሰለፈኞቹ ከአሰሟቸው መፈክሮች መካከል "በውክልና የሚደረግ ጦርነት ይብቃ" "ምዕራባውያን ሉዓላዊነታችንን አክብሩ" "የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው" የሚሉ ይገኙበታል።
እንዲሁም የአዳማ ከተማና አከባቢዋ ሕዝብ "ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ'' በሚል መሪ ቃል የአሸባሪው ህወሓት በሀገር ላይ እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባርና የውጭ ይሎች ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ሰለማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
'ሰልፈኞቹ 'አሸባሪው ሕወሓት ፀረ- ሰላም ቡድን ነው፤ 'ምዕራባውያን ከኢትዮጵያ ላይ እጃሁን አንሱ፤ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ሆነን የሀገራችንን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት እንጠብቃለን! የሚሉ መፈክሮችም እየተስተጋቡ ነው።