አሸባሪውን ህወሃት የሚያወግዝ እና የምዕራባዊያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በሀላባ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪውን ህወሃት የሚያወግዝ እና የምዕራባዊያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ በሀላባ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት 12 ቀን 2015 (ኢዜአ) ”ለኢትዮጵያ እቆማለሁ፤ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል አሸባሪውን ህወሃት የሚያወግዝ እና የምዕራባዊያንን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚያወግዝ ሰልፍ በሀላባ እየተካሄደ ይገኛል።
በሰልፉ ላይ ከሀላባ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አርሶ አደሮችና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ሰልፈኞቹ ምዕራባዊያን በአሸባሪው ሕወሓት ላይ የያዙትን የማይገባ አቋምና በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጫና የሚያወግዙ መፈክሮችን በመያዝ ነው ለተቃውሞ የወጡት።
"በውክልና የሚደረግ ጦርነት ይብቃ"፣ "ምዕራባውያን ሉአላዊነታችንን አክብሩ"፣ "የኢትዮጵያ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ነው" የሚሉ መፈክሮችን በማሰማትና በማንገብ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ሰልፈኞቹ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አክብሮት፣ ድጋፍና አጋርነት በመግለጽ፤ ለሰራዊቱ ምስጋና አቅርበዋል።