ቀጥታ፡

የቡና አምራች ክልሎች ብሔዊ የቡና ምርት የጥራት ንቅናቄ መርሐ ግብር ሊካሔድ ነው

ጥቅምት 11/2015 (ኢዜአ) የቡና አምራች ክልሎች ብሔራዊ የቡና ምርት የጥራት ንቅናቄ መርሐ ግብር ሊካሔድ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ገለጸ።

መርሐ ግብሩ ከጥቅምት 15 ቀን እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ባለስልጣኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሸምሱ የጥራት ንቅናቄ መርሐ ግብሩ ''የቡና ምርት ጥራት ለዘላቂ ዕድገት'' በሚል መሪ ቃል እንደሚካሔድ ገልጸዋል።

መርሐ ግብሩ በሚዛን፣ ጅማና ሐዋሳ እንደሚካሔድ ጠቁመው አምራቾች፣ ላኪ የኢንዲስትሪ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ይሳተፋሉ ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የቡና ጥራትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የሚደረግ ሲሆን የመስክ ጉብኝት እንደሚኖርም ተገልጿል።

በመስክ ጉብኝቱ ላይ የእሸት ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪዎች ዝግጅታቸው የሚጎበኝም እንደሆነም ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም