ቀጥታ፡

በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የሚካሄደው የሰላም አማራጭ በመጪው ሰኞ ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ ተገለጸ

ጥቅምት 10 ቀን 2015(ኢዜአ) በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የሚካሄደው የሰላም አማራጭ በመጪው ሰኞ ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

አምባሳደር ሬድዋን የአፍሪካ ህብረት የሰላም ንግግሩ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 14 በደቡብ አፍሪካ እንደሚካሄድ አሳውቆናል ብለዋል።

No photo description available.

አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት በአፍሪካ ህብረት በኩል ለሚካሄደው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ ያረጋግጣል ነው ያሉት።

ሆኖም አሁንም መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚወስደውን የመከላከል ርምጃ ለማጠልሸት፤ የሃሰት ክስን ለመሰንዘርና የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ በሚጥሩ አካላት ላይ ያለውን ቅሬታ ይገልጻል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም