የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ወገኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው - አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ወገኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው - አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ
ጥቅምት 9/2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ወገኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ።
አንዳንድ ምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ያልተገባ ጫና በማሳደርና የአሸባሪዎችን ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ሲያስተጋቡ ተስተውለዋል።
ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጨምሮ ሌሎችም የልማት ፕሮጀክቶች እንዳይሳኩ የውጭ አካላቱ ከሀገር ውስጥ የጥፋት ቡድኖች ጋር በማበር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም።
በዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ግን የኢትዮጵያን እውነታ ለዓለም ሕዝብ በማሳወቅና ጫናዎችን በማውገዝ ከፍተኛ ርብርብ ያደረጉና አሁንም የቀጠሉ ወገኖችና ወዳጆች በርካቶች ናቸው።
እነዚህ ወገኖች ገንዘብ በማዋጣት አገራቸውን ከመደገፍ ባለፈ በሰላማዊ ሰልፍና በዲጂታል ዘመቻ ጭምር የላቀ ሚናቸውን ተወጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከእናት አገራቸው ጥቅም ጋር የተቆራኘ አኩሪ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።
ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገትና የብልጽግና ጉዞ ድጋፍና እገዛቸውም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።
በኢንቨስትመንት፣ በክህሎትና በሌሎች የልማት መስኮች ላይ በመሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ በማድረግ የነበራቸውን ሚና ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ነው የጠየቁት።
በአውሮፓ፣ በአሜሪካና ሌሎች ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ወዳጆች ለኢትዮጵያ ላበረከቱትና እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ አምባሳደር ተስፋዬ አመስግነዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤