ቀጥታ፡

ምዕራባዊያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በብራሰልስ ሊካሔድ ነው

ጥቅምት 8/2015/ኢዜአ/ አንዳንድ ምዕራባዊያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በቤልጂየም ብራስልስ ሊካሄድ መሆኑን ዲፌንድ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡

በሰልፉ ላይ በቤልጂየም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚሳተፉበት መሆኑ ታውቋል።

የዲፌንድ ኢትዮጵያ የብራስልስ አስተባባሪ ኤፍሬም ዘውዱ፤ የሰልፉ ዓላማ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነባራዊ እውነታውን ለአለም ማህበረሰብ ማሳወቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የተቃውሞ ሰልፉ የፊታችን ሀሙስ በቤልጂየም ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ይካሄዳል ብለዋል።

በቤልጂየም ፓርላማ፣ በአሜሪካ ኤምባሲ እና ሌሎችም ትልልቅ የመንግስት ተቋማት አካባቢ ሰልፉ የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል።

በሰልፉ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና የሚያወግዙ መልዕክቶች እንደሚተላለፉበትም ተገልጿል፡፡

አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚያስገነዝቡ መፈክሮች በሰልፈኞቹ እንደሚንጸባረቁ አስተባባሪው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም