ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን ሰላምን በራሳቸው የመፍጠር አቅም አላቸው - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ

ጥቅምት 8 / 2015 (ኢዜአ) “ኢትዮጵያውያን ሰላምን በራሳቸው ለመፍጠር የሚያስፈልግ አቅም እና ብርታት አላቸው” ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

“የኢትዮጵያውያን ማህበራዊ መስተጋብር የተገነባው በላብ፣ በትግል፣ በድልና በክብር ነው” ብለዋል አምባሳደር ታዬ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

“እኛ ሰላምን ለማምጣት ብርታትና አቅም አለን” ያሉት ቋሚ መልዕክተኛው፤ “ሰላም ለዘመናት አብሮን የቆየውን ማህበራዊ መሰረት እንዲዘልቅ ያደረግንበት የጥንካሬያችን ፍሬ ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም