የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ጎበኙ

ጥቅምት 8 /2015 (ኢዜአ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ጎበኙ።
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፤ የፈተና ሂደቱን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ተመልክተዋል።
በመጀመሪያው ዙር የታዩ ድክመቶችን በማሻሻል ለሁለተኛው ዙር የተሻለ ዝግጅት በመደረጉ እስካሁን ያጋጠመ ችግር አለመኖሩም ተገልጿል።
ዘንድሮ በተለየ ቦታና የፈተና ሂደት በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ያለው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተሳካ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ ታውቋል።
በሁለተኛው ዙር የፈተና አሰጣጥ መርሃ ግብር በ130 የፈተና ጣቢያዎች በሙሉ ፈተና መጀመሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ አረጋግጠዋል።