ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ የልማት ፕሮጀክትን የሥራ ክንውን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ የልማት ፕሮጀክትን የሥራ ክንውን ጎበኙ

ጥቅምት 07 ቀን 2015 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን፣ የገበታ ለሀገር አንድ አካል የሆነውን የጎርጎራ የልማት ፕሮጀክትን የሥራ ክንውን ጎብኝተዋል።

"ገበታ ለሀገር" የተሰኘና ከአዲስ አበባ ውጪ ሶስት ቦታዎች የሚለሙበት ፕሮጀክት ሲሆን ከአማራ ክልል ጎርጎራ፣ ከኦሮሚያ ክልል ወንጪ እንዲሁም ከደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ኮይሻ የፕሮጀክቱ አካል መሆናቸው ይታወቃል።