ሀገር አቀፉ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አውደ-ርዕይ እና አውደ-ጥናት በሚዛን አማን ከተማ ተከፈተ

21

ጥቅምት 4 ቀን 2015 (ኢዜአ) ሀገር አቀፉ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አውደ-ርዕይ እና አውደ-ጥናት በሚዛን አማን ከተማ ዛሬ ተከፍቷል።

በፌደራል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እና የቤንች ማጂ ጫካ ቡና የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን በጋራ የተዘጋጀ ነው።

በአውደ-ርዕዩ የተለያዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የሚያመርቷቸውን የግብርና ምርቶች ለእይታ አቅርበዋል።ለአራት ቀናት በሚቆየው መርሐ-ግብር ላይ የተለያዩ የውጭ ሀገር የቡና ገዥዎችና አምራች ማኅበራት የግብይት ትስስር ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአውደ-ርዕዩ ላይ የቡና፣ የማር፣ የተለያዩ ቅመማቅመሞችና ሌሎች የማኅበራት የግብርና ምርቶች መቅረባቸው ተመላክቷል።

አውደ-ርዕዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የጋራ ተጠቃሚነትና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍን ዓላማ የደረገ መሆኑን የቤንች ማጂ ጫካ ቡና የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ተክሌ ለኢዜአ ገልጸዋል።

አውደ ርዕዩንና አውደ ጥናቱን አቶ ፍቅሬ አማን በፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነትና አስተዳደር ወሰን የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ፍቅሬ አማን የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና አቶ ቀበሌ መንገሻ የዩኒየኑ ስራ አስኬያጅ አቶ ጌታሁን ተክሌ መርቀው ከፍተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም