ከውጭ በሚገቡ 38 ምርቶች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ ገደብ ተጣለ - ኢዜአ አማርኛ
ከውጭ በሚገቡ 38 ምርቶች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ ገደብ ተጣለ
ጥቅምት 4/2015 (ኢዜአ) ከውጭ በሚገቡ 38 ምርቶች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንዳያገኙ ገደብ መጣሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ።
ባንኩ ውሳኔውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
የባንኩ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስት ፍቃዱ ደግፌ እንደገለጹት ቅድሚያ የማይሰጣቸውና ከውጭ ለሚገቡ 38 ምርቶች የውጭ ምንዛሬ እዳይፈቀድ ተወስኗል።
ውሳኔው ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ጠቁመው ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
የውጭ ምንዛሬ እገዳ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ለስራ አገልግሎት የማይውሉ መኪናዎች፣ ሰው ሰራሽ ጸጉር፣ ጌጣጌጦች፣ የቡስኩትና የመሳሰሉ ምርቶቸን ይገኙበታል።
እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚስቱ ተናግረዋል።