ቀጥታ፡

የዘንድሮውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተለያዩ መርሐግብሮች ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል- አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ጥቅምት 04/2015(ኢዜአ) ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር ዝግጅቱ መጠናቀቁን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

የፌዴሬሸን ምክር ቤት የእለቱን አከባበርና አጠቃላይ ዝግጅት በማስመልከት ከመገናኛ ብዙሀን አመራሮች ጋር ተወያይቷል።

የዘንድሮው እለት አገራዊ አንድነትን ማጠናከርን መሰረት በማድረግ በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ህገ-መንግስታዊ እኩልነትና ኅበረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያሳይ መልኩ በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን የሚከበር መሆኑ ይታወቃል።

ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን "ሕብረብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ሃሳብ በሀዋሳ ከተማ ይከበራል።

16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል  ‹‹ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት›› በሚል መሪ  ሃሳብ  በድሬዳዋ ከተማ መከበሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም