የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
ጥቅምት 03 ቀን 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ በትናንትናው ዕለት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት የሞነተሪና ካፒታል ማርኬት ዲፓርትመንት ም/ዳይሬክተርና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም በዲፓርትመንቱና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል በውጭ ምንዛሬ፣ በገንዘብ ገበያ፣ በዲጂታል ገንዘብ፣ በውጭ ባንኮች ሬጉሌሽንና ሱፐርቪዥን እንዲሁም በኢንሹራንስ ዘርፍ ሬጉሌሽን ረገድ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪም አስፈላጊው የቴክኒክ ድጋፍ ስለሚሰጥበት እና በቀጣይ የሥራ ሂደቶች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለኢዜአ የላከው መረጃ ጠቁሟል።