አስር የኢትዮጵያ ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 እየተሳተፉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አስር የኢትዮጵያ ጀማሪ የስራ ፈጣሪዎች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 እየተሳተፉ ነው
ጥቅምት 2 ቀን 2015 (ኢዜአ)አስር የኢትዮጵያ የስራ ፈጣሪዎች (ስታርትአፖች) በዱባይ ጂ አይ ቴክስ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው።
የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና ስታርትአፖች ቡድን በኤክስፖው እየተሳተፈ ነው።
ቡድኑ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚቆየው የዱባይ ቴክኖሎጂና ስታርትአፕ ኤክስፖ ለመሳተፍ ነው ያቀናው።
በኤክክፖው ከ170 በላይ ሀገራት የመጡ ታላላቅ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ስታርትአፖች ይሳተፋሉ፡፡
በኤክስፖው ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና፣ የአይ ሲ ቲ እና የዲጂታል፣ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ አስር ስታርት አፖችን በማሳተፍ ምርትና አገልጎሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እያደረገች ነው፡፡
በዚህም በተለየዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉና ባለሃብቶች ጋር እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡