ቀጥታ፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

መስከረም 27/2015 (ኢዜአ) በ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ሀድያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና ከቀኑ 7 ሰአት እንዲሁም አዳማ ከተማ ከመቻል ከቀኑ 10 ሰአት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ትናንት በተደረጉ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የአምናው የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ ኤሌትሪክን 1 ለ 0 ሲያሸነፍ ድሬዳዋ ከተማና ለገጣፎ ለገዳዲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም