የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ መስከረም 26 / 2015 (ኢዜአ) የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአቀባበል ሥነስርዓቱ ላይ የአገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ የሁለቱን አገራት ትብብር እና ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረት ትብብር ያላቸው አገራት ናቸው።