በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
መስከረም 26 /2015 (ኢዜአ) በ2015 በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከቀኑ 7 ሰአት ኢትዮ ኤሌትሪክ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ከቀኑ 10 ሰአት ለገጣፎ ለገዳዲ ከድሬዳዋ ከተማ ይጫወታሉ።
ትናንት በተደረጉ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0፤ ኢትዮጵያ መድን አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 3 አሸንፈዋል።
ነገ ከቀኑ 7 ሰአት ሀዲያ ሆሳዕና ከሲዳማ ቡና፤አዳማ ከተማ ከመቻል ከቀኑ 10 ሰአት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።