የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት 49 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

124

መስከረም 25/2015 (ኢዜአ) የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት 49 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ለመከላከያ ሚኒስትር ድኤታ ማርታ ሉዊጂ አስረክበዋል፡፡

ከንቲባ በዚሁ ጊዜ የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ለሰራዊቱ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለት ደግሞ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች በማሰባሰብ የ30 ሚሊዮን ብር እና 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡

ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ  ኢትዮጵያዊያን ለአገር ህልውና መጠበቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታቸውን በተግባር እያረጋገጡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ላደረገ ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ዴኤታዋ ኢትዮጵያዊያን ለሰራዊቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም