በኢትዮጵያና ቆጵሮስ የንግድ ግንኙነት የሚያጠናክር የቢዝነስ ፎረም ለማዘጋጀት ስምምነት ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያና ቆጵሮስ የንግድ ግንኙነት የሚያጠናክር የቢዝነስ ፎረም ለማዘጋጀት ስምምነት ተካሄደ
መስከረም 23 ቀን 2015(ኢዜአ) የኢትዮጵያና ቆጵሮስ ሪፐብሊክን የንግድ ግንኙነትና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር የሚያስችል የቢዝነስ ፎረም ለማዘጋጀት ስምምነት ተካሄደ።
አምባሳደር ደሚቱ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ስለአለው ሁኔታ ገለፃም አድርገዋል።
አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከቆጵሮስ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ቴሳላ ሳሊና ሻምቦስ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደሯ ከዳይሬክተሯ ጋር በሁለትዮሽና በወቅታዊ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ነው ውይይት ያደረጉት።
የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በኢንቨስትመንትና በንግድ መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮችም በውይይቱ ተነስቷል።
በቀጣይ የኢትዮጵያ-ቆጵሮስ ቢዝነስ ፎረም በማዘጋጀት ግንኙነቱን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መደረሱን በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።
አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከቀናት በፊት በቆጵሮስ ሪፐብሊክ 62ኛ አመት የነፃነት በዓል ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ሲሆን ለሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኒኮስ አናስታሲታደስ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማቅረባቸው ይታወሳል።