በጣሊያን የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ - ኢዜአ አማርኛ
በጣሊያን የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ

መስከረም 22 /2015 (ኢዜአ) በጣሊያን ትሬንቶ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በውድድሩ በወንዶች የዓለም ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ሲያሸንፍ በሴቶች ደግሞ ብሩክታይት ደገፋው ድል ቀንቷታል።
በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድርም እንዲሁ ሙክታር ኢድሪስ ማሸነፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።