አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በለንደን ማራቶን አሸነፈች

294

መስከረም 22 ቀን 2015 (ኢዜአ) አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ዛሬ የተካሄደውን የለንደን ማራቶን ውድድር አሸነፋች፡፡

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በለንደን ማራቶን 2:17:26 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ጨርሳለች።

ኬንያዊቷ አትሌት ጆይሲሊን ጄፕኮስጌይ በውድድሩ 2:18:07 በሆነ ሰዓት 2ኛ ስትወጣ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መገርቱ ዓለሙ ደግሞ 2:18:32 በሆነ ሰዓት 3ኛ ወጥታለች።

በተመሳሳይ በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረሥላሴ በ 2:05:12 በሆነ ሰዓት 2ኛ ወጥቷል።

ውድድሩን ኬንያዊው አትሌት አሞስ ኪፕሩቶ 2:04:39 በሆነ ሰዓት 1ኛ በመውጣት አሸንፏል።

ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌት ክንዴ አጣናው 4ኛ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 5ኛ፣ አትሌት ብርሃኑ ለገሰ 6ኛ እና አትሌት ሲሳይ ለማ 7ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም