የሲዳማ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት 26 ሚሊዮን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የሲዳማ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት 26 ሚሊዮን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

መስከረም 20 / 2015 (ኢዜአ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት የ26 ሚሊዮን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየታገለ ለሚገኘው ጀግናው ሰራዊታችን ለአበረከታቹት አስተዋጽኦ ክብር አለን ብለዋል።
የሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ሃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችን ለማሳየት 20 ሚሊየን የገንዘብና 6 ሚሊየን የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።