ቀጥታ፡

አምባሳደር ስለሺ በቀለ በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙርያ ከአሜሪካ የሴኔት ደህንነት ጉዳዮች ሰብሳቢ ማርክ ዋርነር ጋር ተወያዩ

መስከረም19/ 2015(ኢዜአ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በወቅታዊ ሁኔታዎች ዙርያ ከአሜሪካ የሴኔት የደህንነት ጉዳዮች ሰብሳቢ ማርክ ዋርነር ጋር ውይይት አካሄዱ።

አምባሳደር ስለሺ ከሴናተር ዋርነርጋር በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት፣ የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በልማቱ ዘርፍ ዳያስፖራው ያለውን ሚና በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ሴናተር ማርክ ዋርነር ከእ.አ.አ 2008 ጀምሮ በሴናተርነት በማገልገል ላይ ሲሆኑ እ.አ.አ ከጥር 2021 አንስቶ የሴኔቱ የደህንነት ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው በመስራት ላይ ናቸው።

በተያያዘ ዜና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ በአገሪቷ ከሚኖሩ ከ200 በላይ ዳያስፖራዎች ጋር ውጤታማና ጠቃሚ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

May be an image of 15 people, screen, television and text

ውይይቱ ዳያስፖራው የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነት በማጠናከር፣ኢትዮጵያን በመደገፍና በልማት ስራዎች እየተወጣ ያለውን ሚና በተመለከተ ብለዋል።

አምባሳደር ስለሺ በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለአገራቸው እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው አሁንም ይበልጥ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም