“ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

245

መስከረም 18 ቀን 2015 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ለገቡት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ አቀባበል አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም “ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ” ብለዋል።

''ኢትዮጵያ በሚኖርዎት የሁለት ቀን የሥራ ጉብኝትዎ በደስታ ትቀበልዎታለች''ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በግንቦት 2014 ዓ.ም በተካሄደው የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ተከትሎ በሰኔ ወር ላይ በተከናወነው የፕሬዝዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም