የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

136

መስከረም 18/2015 (ኢዜአ) የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በግንቦት 2014 ዓ.ም በተካሄደው የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል።

በሰኔ ወር ላይ በተከናወነው የፕሬዝዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተገኝተው መልእከት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የትብብር ግንኙነትና ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው አገሮች መሆናቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም