ሩሲያና አሜሪካን ጨምሮ የ18 አገራት ኤምባሲዎች ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 17 ቀን 2015(ኢዜአ) ሩሲያና አሜሪካን ጨምሮ የ18 አገራት ኤምባሲዎች ለክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶቻችን በዓሉ የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል።በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የመስቀል በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆንምኞቱንገልጿል።

ካናዳ፣ሕንድ፣እስራኤል፣ዩናይትድኪንግደም፣ፈረንሳይ፣ጣልያን፣ጀርመን፣ኔዘርላንድስ፣ዴንማርክ፣ስዊዘርላንድ፣ግብጽ፣ሞሮኮ፣አልጄሪያ፣ኢራን፣ፓኪስታንና ሜክሲኮ ሌሎች የበዓል መልካም ምኞታቸውን የገለጹ አገራት ናቸው።

የመስቀል በዓል በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

ትናንት የመስቀል ደመራ በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ ስርአት መከበሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም