ቀጥታ፡

የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል

መስከረም 17 ቀን 2015 (ኢዜአ) የመስቀል በዓል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዓሉ በተለያዩ ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ ሥነ ስርአቶች በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በትናንትናው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል በመላ ሀገሪቱ በደማቅ ሥነ ስርአት መከበሩ ይታወሳል።

May be an image of 4 people and outdoors

በተለይም በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምዕመናን እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም