የመስቀል ደመራ በዓል በኳታር ዶሃ እየተከበረ ነው

110

መስከረም 16 /2015 (ኢዜአ) የመስቀል ደመራ በዓል በኳታር ዶሃ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት በኳታር የኢፌዴሪ ልዩ መልእክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፌይሰል አልይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አምባሳደሩ በመልዕክታቸው ለመላው የኤምባሲው ሠራተኞች እና በኳታርና በመላው አለም ለምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለ2015 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሠላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በዓሉ የመተሳሰብ፣ ችግሮችን በጽናት የማለፊያ፣ የፍቅር እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በበዓሉ ላይ የኤምባሲው ሠራተኞች እና በኳታር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች መገኘታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም