በዓሉ የሰላምና አንድነት እንዲሆን እመኛለሁ-ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

22

መስከረም 16 / 2015 (ኢዜአ) የመስቀል በዓል የሰላምና አንድነት እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም በዓሉ የሰላምና የአንድነት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚከበረው የሽናሻ ብሄር ዘመን መለወጫ ወይም "ጋሪ-ወሮ " በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም